






የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ የተገነባውን የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከልና በወረዳው የተገነባውን የአስተዳደር ህንፃ መርቀው ከፍተዋል።
በማሪ ማንሳ ወረዳ ማሪ ከተማ የተገነባው የቁም እንስሳት የግብይት ማዕከል በአካባቢው ካለው የእንስሳት ዕምቅ ሀብት የሚመነጨውን ኢኮኖሚ በአግባቡ ለመጠቀም የሚያግዝ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
አካባቢው በእንስሳት ሀብት፣ በእርሻና በንግድ የሚታወቅ ቢሆንም ዘመናዊ ግብይት ማዕከሉ ባለመኖሩ የዘርፉ ተጠቃሚነት ሳይረጋገጥ መቆየቱን አንስተዋል።
በመሆኑም በወረዳው የተገነባው የግብይት ማዕከል ዘመናዊ የእንስሳት ግብይት ኢንዲኖር በማድረግ ከወርፉ ከሚመነጨው ኢኮኖሚ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችለዋል ብለዋል።
በአካባቢ የሚመረቱ የተለያዩ ምርቶችን ወደ ዘመናዊ መቀየር እንደሚገባ የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳደሩ ከመሠረት ልማት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች እየተፈቱ መሆናቸውን በመግለጽ በቀጣይ ተራ በተራ የሚሰራበት ሁኔታ እንደሚመቻች ተናግረዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ለሁለንተናዊ ብልጽግና መሠረት የሚጥሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችንና የልማት አውታሮችን መስራት መቻሉን በመግለጽ ብልጽግናን በመምረጥ የተጀመሩ ለውጦችን እንዲያስቀጥሉ አሳስበዋል።
የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ በበኩላቸው፤ ክልሉም ሆነ ወረዳው በእንስሳትና በእንሳት ምርቶችን በማቅረብ ክልል እንደሚታቅ በማንሳት ዘርፉን ለማዘመን ማዕከሉ መገንባቱን አንስተዋል።
የአካባቢው ህዝብ በንግድ እንቅስቃሴና ተሳትፍ ሌሎች አካባቢዎች እንደተሞክሮ የሚወሰድ በመሆኑ የግብይት ማዕከሉ ብዙ ተወኒያንን ከተለያዩ አካባቢዎች በማሳተፍ የገበያ ትስስርና መነቃቃት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
የዳውሮ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ የገበያ ማዕከላትን በማዘመን ሻጭና ገዥ በቀጥታ በማገናኘት በመሀል የሚፈጠረውን ደላላና ገበያ አሻጥርን በማስወገድ የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እንደሚረዳ ተናግረዋል።
የማሪ ማሪ ማንሳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዳመኔ ዳዋና በወረዳው የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ከመመለሱም ባሻገር ወረዳው የብልጽግና ትሩፋት መሆኑን ገልጸዋል።
በወረዳው የውስጥ ገቢ ተመርቀው ለአገልግሎት የበቃው ስራ መልካም መሆኑን በማንሳት መሰል ተግባራት ተጠናክሮ እንዲጥሉ ተመልክቷል።
በጌታሁን ግርማ
