በትናንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ሰባተኛው ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና ሥነሥርዓት ተካሂዷል።

Spread the love

በ2010 ዓመተ ምህረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረው ይኽ ሥነሥርዓት የዜግነት የግብር ግዴታቸውን በወቅቱ እና በታማኝነት የሚፈፅሙ ዜጎችን ለማበረታታት ታቅዶ የሚተገበር ነው።

በዘንድሮው መርሃ ግብር 700 ታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ተሰጥቷቸዋል። በ2017 ዓመተ ምህረት እንደነበራቸው አስተዋጽኦ መጠን 105 የፕላቲኒየም ደረጃ፣ 245 የወርቅ ደረጃ፣ 350 ደግሞ የብር ደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል። የጋራ አስተዋጽኦዋቸው በሥራ ዘመኑ 900.22 ቢሊዮን ብር በግብር እንዲሰበሰብ አስችሏል።

በተጨማሪም የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን በግብር እና ቀረጥ አሰባሰብን ብቁ እና ግልፅ የሚያደርጉ የዲጂታል ሥርዓቶችን አስጀምረዋል። ከነዚህም ውስጥ የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት፣ ኤሌክትሮኒክ የጉምሩክ አስተዳደር ሥርዓት እና ኤሌክትሮኒክ የጭነት መከታተያ ሥርዓት ይገኙበታል።

#PMOEthiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *