የሴቶች የልማት ኅብረት አደረጃጀት በማጠናከር ለላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መትጋት እንደሚገባ ተገለጸ።

Spread the love

የሴቶች የልማት ኅብረት አደረጃጀት በማጠናከር ለላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መትጋት እንደሚገባ ተገለጸ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሴቶች የልማት ኅብረት የቴክኒክ ኮሚቴ ውይይት በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።

በኅብረቱ አደረጃጀት ተግባርና ዝርዝር ኃላፊነት ላይ ሰነድ ያቀረቡት የክልሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሪት ለምለም አምሳሉ፥ አደረጃጀቱን በማጠናከር ለላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት መትጋት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለሁለንተናዊ ልማት እና ማህበረሰብ ተጠቃሚነት መረጋገጥ የሴቶች የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መኾኑን የጠቆሙት ወ/ሪት ለምለም በዚህም ረገድ አደረጃጀቱ የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

የሴቶች የልማት ኅብረት አደረጃጀትን በማጠናከር በክልሉ ሁለንተናዊ ልማት ግምባር ቀደም ተዋናይ በማድረግ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባም ነው ኃላፊዋ የገለጹት።

ሴቶችን በሁሉም የልማት ዘርፍ በንቃት ማሳተፍ አንኳር ጉዳይ መኾኑን ያነሱት ወ/ሪት ለምለም ለዚህም ስኬት የባለድርሻ አካላት የበጀት ፣የሰው ኃይልና የግብዓት ድጋፍ ማሳለጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አደረጃጀቱን በየደረጃው እንደገና የማጠናከር እና መልሶ የማደራጀት ተግባር እንደሚከናወን የገለጹት ኃላፊዋ በዚሁም የደረሰበት የተግባር አፈጻጸም በየጊዜው እየተገመገመ የምዘና ስርዓት ተፈጻሚ እንደሚሆን ተናግረዋል።

በቀጣይም የክልሉ የሴቶች የልማት ኅብረት ቴክኒክ ኮሚቴ ተቋማት ዕቅድ በማዘጋጀት እንዲሁም ድጋፍና ክትትል ስርዓት በመዘርጋት ለአደረጃጀቱ ውጤታማነቱ መረጋገጥ ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።

የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በበኩላቸው የአደረጃጀቱን ተልዕኮ በላቀ ተነሳሽነት ለመፈጸም ቁርጠኛ መኾናቸውን በመግለጽ ተግባሩ በታችኛው መዋቅር ውጤታማ እንዲሆን ድጋፍና ክትትል ሥራው መጠናከር እንዳለበት አንስተዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *