አመራሩ ለፓርቲው ተልዕኮ መሳካት በላቀ ቁርጠኝነት ራሱን ማዘጋጀት አለበት። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

አመራሩ ለፓርቲው ተልዕኮ መሳካት በላቀ ቁርጠኝነት ራሱን ማዘጋጀት አለበት። ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ‎የ2017 በጀት ዓመት የተግባር አፈጻጸምን መነሻ ያደረገ ክልላዊ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ ተካሄዷል።

የአመራር ግምገማና ምዘናው በፓርቲው መርህ፣ ፓርቲው በረዥምና መካከለኛ ዘመን ማኒፌስቶ መሠረት ለህዝብ የተገባው ቃል አፈጻጸም እንዲሁም የተቋማት ተልዕኮ እና ውጤት መነሻ ያደረገ መኾኑ ተጠቁሟል።

የምዘናና ግምገማ አስፈላጊነቱ ፓርቲው የያዘውን ጠንካራ እና ቅብልነት ያለውን ሀገረ መንግሥት በመገንባቱ ረገድ÷ነጻ፣ ጠንካራ እና ብቃት ያለውን ተቋም ለመገንባት አመራር የተጣለበትን ኃላፊነት ከመወጣት ረገድ ለመመዘን መኾኑም እንዲሁ።

አመራሩ ለፓርቲው ተልዕኮ መሳካት በላቀ ቁርጠኝነት ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ያስገነዘቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) አሰባሳቢ ትርክቶችን በማጉላት ለክልላዊ አንድነት አስተዋጽኦ ማበርከት አለበት ብለዋል።

አመራሩ ስትራቴጂክ በመኾን የህዝብ የልማት ጥያቄዎችን በተገቢው መመለስ፣ በተቋማ ውስጥ ፓርቲን የመትከል እንዲሁም ራሱን ከብልሹ አሰራር በማጽዳት አርዓያ መኾን እንዳለበትም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ ያስገነዘቡት።

በተቋማት ውስጥ የፓርቲና የመንግስት ተልዕኮ በመፈጸምና በማስፈጸም ረገድ አመራሩ የሚስተዋሉ ውስንነቶችን ፈጥኖ በማረም የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅበትም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በአመራር ግምገማ መነሻ ቀጣይ በሚወስዱ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ እርምጃዎች አመራሩ ራሱን ዝግጁ እንዲያደርግ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል::

የአመራር ምዘናና ግምገማው የሚስተዋሉ ችግሮችና ድክመቶች በተገቢው ያሳየ እንደነበረ የገለጹት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሬ አማን ከግምገማው መነሻ ቀጣይ የማረም ሥራ ይሰራል ብለዋል።

አመራሩ ችግሮችን ከመላመድ በመውጣት ራሱን ለመለወጥ መዘጋጀት እንዳለበት የገለጹት አቶ ፍቅሬ በተቋማት ውስጥ የብልጽግና ኅብረት መድረኮችን በመምራትና በመሳተፍ ፓርቲን መትከል እንደሚገባ ተናግረዋል።

በግምገማው ነጥሮ የወጡ ብልሽቶችን ፈጥኖ በማረም እንደሚገባም አቶ ፍቅሬ ያስገነዘቡት።

በዕድገቱ በዛብህ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *