በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሁሉም ዞኖች የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የአጠቃላይ አመራር አካላት ግምገማ እና ምዘና መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።




በዞኖች የተጀመረው የአጠቃላይ አመራር አካላት ግምገማ እና ምዘና በአመለካከት፣ በስነምግባር፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ፤በተግባር አፈጻጸምና ዉጤታማነት ላይ ዓላማ ያደረገ መድረክ ነዉ።
ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት በሀገሪቱ የተለያዩ ፈታኝ ሁኔታዎችን እያለፈ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን እያስመዘገበ የሚገኘውን ውጤት ቀጣይ ለማድረግ አመራሩ ግንባር ቀደም ሚና እንዲወጣ ወቅታዊ የግምገማ እና ምዘና መድረኮች ወሳኝነት እንዳላቸውም ተመላክቷል።
የግምገማና ምዘና ስርዓት ዋና ዓላማው ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ራዕይን እውን የማድረግ ዓላማን ያነገበ ሲሆን ይህም የአመለካከት ጥራት፣የታነፀ ስነ ምግባር የተላበሰ፣ በእውቀት እና በአፈፃፀም የበቁ እና የላቁ አመራርን ለመፍጠር ምቹ መደላድል እንደሚፈጥርም ተጠቅሷል።
ምዘናው በአፈጻጸም ወቅት የሚታዩ ችግሮችን የሚፈታ ፣የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፣በየአካባቢው ያሉትን የህዝቡን የልማት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ሊያጎላ የሚችል እርስ በእርስ የመገነባቢያ መድረክ ጭምር ነዉ።
በፍቅር ከበደ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
