የዘንድሮ የ”ቶክ ቤአ” በዓል በተሻለ ሁኔታ ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል_ አቶ ፍቃዱ ደምሴ

Spread the love

የዘንድሮ የ”ቶክ ቤአ” በዓል በተሻለ ሁኔታ ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል_ አቶ ፍቃዱ ደምሴ

“ቶክ ቤአ” የዳውሮ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን በየአመቱ በነሀሴ ወር መጨረሻና በጳጉሜ ወር መግቢያ ቀናት አከባቢ በድምቀት ይከበራል።

በዚህም የ2017 ዓ.ም የቶክ ቤአ በዓል በድምቀት ለማክበር በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ከሚዲያችን ጋር ቆይታ ያደረጉ የዳውሮ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ደምሴ ተናግረዋል።

የዘንድሮ በዓል በነሀሴ 29/2017 በሚደረገው የጎዳና ላይ ትርዕትና ክዋኔ ተጀምሮ ነሀሴ 30/2017 በፓናል ውይይት እንዲሁም ጳጉሜ 01/2017 በታርጫ ሁለገብ ስታዲየም እንደሚከበርም ሀላፊው አስረድተዋል።

በበዓሉ ከፌደራል ጀምሮ በርካታ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የአጎራባች ዞኖች አመራር አካላት እንዲሁም መላው የዞኑ ተወላጆችና ወዳጆች እንዲሳተፉ ጥሪ መተላለፉንም አንስተዋል።

የ”ቶክ ቤአ” በዓል ህዝባዊ መሠረት ይዞ እንደሚከበር የገለፁት ሀላፊው በዓሉ ከቀበሌ መዋቅር ጀምሮ ከፍ እያለ እንደሚመጣም አስረድተዋል።

በበዓሉ አከባበር ዙሪያ ከሀይማኖት ፎረሞችና ከአገር ሽማግሌዎች ጋር እንዲሁም ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች መደረጉንም አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል።

ባህል ሁሉም ነገር ነው ያሉት አቶ ፍቃዱ ባህልን ማክበር የራስ ማንነት ማክበር እንደሆነም አስገንዘበዋል።

በበዓሉ የአሁኑ ትውልድ ከትላንት ትውልድ የሚማሩት በርካታ ነገሮች እንዳሉ የገለፁ ሀላፊው የበዓሉ መከበር አዎንታዊ ልምዶችንና ወጎችን እንዲሁም የባህል እሴቶችን ለትውልድ ለማስተላለፍ ያስችላልም ማለታቸውን የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

የ”ቶክ ቤአ” በዓልን የባህል መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ያሉት የመምሪያው ሀላፊ ከክብረ በዓሉ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በሚኖረው የፓናል ውይይት በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተዘጋጀው ጥናታዊ ፅሁፍ ለውይይት ይቀርባልም ብለዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *