




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአመራር ቡድን በዳውሮ ዞን የድጋፍና ክትትል ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል ።
በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመሠረተ-ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ የተመራው የአመራር ቡድን በዳውሮ ዞን የተቀናጀ የድጋፍ እና ክትትል ሥራዎች እያደረጉ ይገኛሉ።
በዚህ ወቅት እንደገለጹት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የየተቋማቱን ሥራዎች በአግባቡ በመለየት እና በመከፋፈል ተግባራትን በቅንጅትና በዉጤታማነት መሥራት ይገባቸዋል።
በቀጣይም የፓርቲና የመንግሥት ተልዕኮዎችን ለማሳካት ምቹ ሁኔታ የምንፈጥርበት ወቅት በመሆኑ አመራሮች በከፍተኛ ጥረትና ትጋት የየዕለት ተግባራትን በብቃት መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የፓርቲ እና የመንግሥት እቅድ አፈጻጸም ጥንካሬና ጉድለት በመለየት ጉድለቶችን ፈጥኖ ማስተካከያ በማድረግ እና ወቅታዊ ተግባራት በእቅዳቸው መሰረት ማሳካት ያስፈልጋልም ሲሉ የገለጹት ደግሞ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሄም ዳንኤል ናቸው።
በባለፈው ጊዜያት በግብርና፣ በጤና፣ በፀጥታ፣ በትምህርት ፤ በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በገቢ፣ በማዕድን፣ በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የክረምትና በጋ በጎ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን፣ በፓርቲ ተግባራት የህንጻ ግንባታ የሃብት አፈጻጸም፣ የአባላት አደረጃጀት፣ አፈጻጸም ዙሪያ ያሉበትን ሁኔታ እና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ በዳዉሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዮብ ቶማስ ሪፖርት ቀርቦ ተገምግሟል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው ባለፉት ወራት የተከናወኑ የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራቶችን አፈፃፀም በጥንካሬ የተገመገመው በማጠናከር ትኩረት የሚሹ ተግባራቶችን ፈጥኖ ማረም እንደሚገባም ገልጸዋል።
ወቅታዊ የፓርቲ እና የመንግሥት እቅዶች ለማሳካት የፓርቲ፣ የመንግሥትና የህዝብ አቅሞች አቀናጅቶ መጠቀም ለውጤት የሚያበቃ በመሆኑ ትኩረት አድርጎ መሥራት እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪ ተናግረዋል።
የፓርቲና የመንግሥት አደረጃጀቶች በማጠናከር የተግባር ማሳኪያ በማድረግ አሠራርና መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ ይገባናልም ብለዋል።
የዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መላኩ ተረፈ የአመራሩ የድጋፍ አግባብ ከውጤታማነት ጋር የሚተሳሰር መሆኑን የነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም ችግሮች መፍታት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የአመራራችን እና የአባላቶቻችን የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ከምንጊዜውም በላይ በማሳደግ የተቀመጡ ግቦች በተገቢው የማሳካት ጉዳይ ቁልፍ ተልዕኮ እንደሆነም አስገንዝበዋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
