



የጸረ_ሙስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ በበዓሉ ተሳታፊ ተማሪዎች ጠይቀዋል።
በክልሉ አለምአቀፍ የሙስና ቀን በተከበረበት የተገኙ ተማሪዎች ሙስናን ለመከላከል በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል ።
ተማሪ በእምነት አትርሳው፣ ተማሪ ኤርሚያስ ቆጭቶና ተማሪ መልካሙ በለጠ ከሸኮ፣ከጉራፈርዳ እና ከሚዛን አማን ከተማ ካሉት ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲሆኑ ሙስናን ለመከላከል በትምህርት ቤት ደረጃ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።
በርካታ ወጣቶች በትምህርት ቤቶች በሚቋቋሙ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ክበባት በመሳተፍ በሙስና መከላከል ስራ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል ።
በትምህርት ገበታ በሰዓቱ መገኘት፣ ኩረጃን በመጠየፍና ከመምህራን ጋር አባታዊ ግንኙነት በመፍጠር በሙስና መከላከሉ ስራ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ባለሙያ የሆኑት አቶ ገብረዮሐንስ አብርሃ ሙስናን ለመከላከል በትምህርት ቤቶች ክበባትን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
በርካታ ወጣቶች በትምህርት ቤቶች እንደሚገኙ የገለጹት ባለሙያው ተከታታይነት ያለውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በተማሪዎች ላይ መስራት ይገባልም ብለዋል።
በክልሉ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የትምህርትና ስልጠና ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ትብለጥ እንግሊዝ ሙስናን ለመከላከል ከትምህርት ቤቶች ጋር በትብብር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ወጣቶች ለብዙ ነገሮች ተጋላጭ መሆናቸውን የገለጹት ባለሙያዋ ሙስናን በመጠየፍና ተዋናይ ከመሆን ወጣቶች እንዲታቀቡ አመለካከትና አስተሳሰብ ላይ የተጀመረው ስራ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።
በታጠቅ አበበ
