ተጠናቅቆ ለአገልግሎት የበቁና ቀጣይ የሚገነቡ ፕሮጀክቶች የብልጽግና ፓርቲ ለህዝብ ጥያቄ የሰጠዉ ምላሽ ማሳያ ናቸዉ፦ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

የህዝብን የልማት ጥያቄ በተገቢው መንገድ ለመመለስ በክልሉ መንግስት የተጀመሩ የተለያዩ ልማት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን የገለጹት በዳውሮ ዞን ኢሳራ ባሌ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ መሠረተ ድንጋይ ባኖሩበትና ግንባታው የተጠናቀቀውን የተለያዩ የልማት ስራዎችን መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው።

ባለፉት ዓመታት የተሰጡ የቤት ስራዎች ተጠናቅቆ እየተመረቁ መሆኑን ያመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ የተጀመሩ ስራዎችን በቀጣይ አጠናክሮ ለመቀጠል ህዝቡ ከብልጽግና ፓርቲ ጎን አንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት የበቁ ፕሮጀክቶች የብልጽግና ፓርቲ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ የሰጠበት ማሳያ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።

ኢሳራና አካባቢው በተፈጥሮ ፀጋ የታደለና ለሰብልም ሆነ ለእንስሳት ዕርባታ ምቹ መሆኑን በማንሳት፤ የህዘብ ለህዝብ ትስስርን በማጠናከር በወረዳው በስንዴ እና በሌሎች የመጡ የልማት ስራዎች ማላቅ እንደሚገባ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና የመንገድ ልማትና ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ እንዳሉት፤ ቢሮው የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በዛሬዉ ዕለትም ከ160 ሚለየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተመረቁ መንገዶችን በዘላቂነት ለመጠቀም የተሰሩ መንገዶችን በመጠበቅና በመንከባከብ እንደሚገባ አቶ ፋጂዮ አሳስበዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ዛሬ መሠረተ ድንጋይ የተቀመጠው ሆስፒታል የክልሉ መንግስት የጤና መሠረተ ልማት ተደራሽነት ችግር ለመፈታት የጀመረውና የብልግና ፓርቲ ቃልን በተግባር ማሳያ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል ።

በ346.8 ሚለየን የሚገነባው የኢሳራ ባለ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሲጠናቀቅ የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት የረዥም ጊዜ የህብረተሰብን ጥያቄ የሚመልስ መሆኑን አንስተዋል።

የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ዛሬ የተመረቁ መንገዶች በአካቢው የሚመረቱ እንደ ጤፍና ፍራፍሬ ምርቶችን ወደ ገበያ ለመውሰድና እናቶችን በፍጥነት ወደ ህክምና ተቋማት ለማድረስ እንደሚያግዝ ገልጸዋል።

የ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የተሳካ እንዲሆን በየደረጃው ያለው አመራር ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጡ ርዕሰ መስተዳድሩ መመሪያ ሰጥተዋል።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *