በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ 7ኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ የምርጫ አስመልክቶ የቅስቀሳ እና የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Spread the love

በመድረኩ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገዛኸኝ ገዝሙ ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ስርዓት በወለደው ጭቁን አስተዳደር በወለዳቸው በተለያዩ ችግሮች ተቀፍድዳ በመያዝ ድህነት ውስጥ የነበረች ሀገር ስለመሆኗ አስረድተው እነኚህ ችግሮች አንገብግበው የተወለደው ብልፅግና ፓርቲ ፈተናዎችን ወደ ዕድልና ድል በመቀየር በፍትሐዊነት ሁሉአቀፍ ዕድገት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል።

“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሃሳብ በቀጣይ ጊዜያት በአፍሪካ ብሎም በዓለም የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተሰራ በመሆኑ ይህም እውን እንዲሆን ‘ብልፅግናን ይምረጡ’ ብለዋል።

‘ፓርቲያችን ብልፅግና’ ከውጭ ሀገር ጥገኝነት ለመላቀቅ የውስጥ አቅም በመገንባትና ከተረጅነት ለመላቀቅ እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ ገዛኸኝ በከተማው የተጀመሩ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ብሎም ሌሎች መሠረተ ልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ በመሆናቸው እነኚህን ስራዎች ለማስቀጠል ‘በስንዴ ነዶ’ ምልክት የተወከለውን ብልፅግና ፓርቲ ይምረጡ ብለዋል።

የአመያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ደጀኔ በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ስርዓቶች የተፈጠሩ ስህተቶችን ለማረምና አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅ ኢትዮጵያን ወደ ሁሉ አቀፍ ብልፅግና እየመራ ነው ብለዋል።

በዚህም በአጭር ዓመታት ሰፊ ተጨባጭና ተስፋ ያፈነጠቁ ተግባራት ተከናውኗል ያሉት አቶ ተመስገን በቀጣይ ጊዜያትም ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

በከተማው የተጀመሩ የኮሪደር፣ የመሠረተ ልማትና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ህዝቡ ብልፅግና ፓርቲን እንዲመርጥ ጥሪ አቅርበዋል።

በመድረኩ የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ዕጩዎች የዳቦ ቆረሳና የርችት መለኮስ መርሃ ግብር አካሂደዋል ሲል ዘገባው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *