


የሸካ ዞን ቴፒ ከተማ አስተዳደር የቤት ለቤት የቤተሰብ ጤና ቡድን ተግባር ይበልጥ ለማጠናከር ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የውይይት መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሂዷል
የቴፒ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዮሐንስ በንዲ በመድረኩ እንደገለጹት የከተማውን ህዝብ ጤናን በመጠበቁ ረገድ በሚሰሩ ስራዎች ሁሉ ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት አደርገው እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ጤናው የተጠበቀ ህብረተሰብን በመፍጠር የልማት ስራውን በማሳለጥ ለራሱን ለሀገሩ የሚበቃ ዜጋ መፍጠር የመንግስት ትኩረት አቅጣጫ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባ ይህን ከግምት በማስገባት ህብረተሰቡ የዚህን በጎ ሀሳብ ከጤናው ግብረ ሀይል ጎን በመቆም የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል።
የቴፒ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ የትምወርቅ አራጌ በበኩላቸው ቤት ለቤት የሚሰራው የቤተሰብ ጤና ቡድን የተሻለ የጤና አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ለማምጣት መሆኑን ተናግረዋል።
የቤት ለቤት የጤና አገልግሎት አሰጣጥ አቅም የሌላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረገና ሌሎች በርካታ ስራዎች አንደሚሰራ የገለጹት ኃላፊ የከተማ ጽዳት ሁኔታን ክትትል ማድረግና ጽዱ ከተማን መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ክትትል አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል ።
የሸካ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ ካይቶ ህብረተሰቡ ጤናውን በሚመለከት በአቅራቢያ ወደ ሚገኘው ጤና ተቋማት በመሄድ የጤናውን ሁኔታ ክትትል ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነና አሁን የተጀመረው የጤና ቡድን ስራ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ገልጸዋል ።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት ይህ በጎ ሀሳብ የሚደገፍ መሆኑንና ከመንግስት ጎን በመቆም የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የሸካ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው።
