የቱሪዝም ማስተር ፕላኑ በዘርፉ ዘላቂነት ያለው አቅም ለመፍጠር የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ ነው

Spread the love

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን በቀጣናው በዘርፉ ቀጣይነት ያለው አቅም ለመፍጠር የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ መሆኑን የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ(ዶ/ር) ገለጹ።

የኢጋድ አባል ሀገራት የቱሪዝም ሚኒስትሮች በማስተር ፕላኑ ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምረዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣናው ያለውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለማሳደግ ከኢጋድ አባል ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ ናት ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለኢጋድ ዘላቂ የቱሪዝም ማስተር ፕላን በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ማስተር ፕላኑ በቀጣናው ዘላቂነት ያለው የቱሪዝም አቅም ለመፍጠር እየተደረገ ባለው ጥረት ውስጥ ወሳኝ የተግባር እርምጃ መሆኑን አመልክተዋል።

የኢጋድ አባል አገራት ለማስተር ፕላኑ ውጤታማነት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሚኒስትሮቹ የቱሪዝም ማስተር ፕላኑ ላይ ውይይት በማድረግ ነገ ያፀድቁታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢጋድና ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ኢሲኤ) ጋር በመተባበር የዓለም ቱሪዝም ቀንን በማስመልከት የተለያዩ ዝግጅቶችን እያካሄደ ይገኛል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *