



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፓርቲና የመንግስት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በክልሉ በስድስት ወራት ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና የመንግስት አፈፃፀሞችን ሪፖርት ያቀረቡት የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ በመንግሥት በአጋር አካላት ድጋፍና በህብረተሰቡ ተሳትፎ የመንገድ የውሃና የመስኖ መሰረተ ልማቶች ተጠናክሮ እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀዋል።
በህብረተሰቡ ለመሰረተ ልማት ግንባታ በገንዘብ በጉልበትና በአይነት ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ገልፀው በስድስት ወር ብቻ ለመንገድ መሰረተ ልማት ህብረተሰቡ ከ221 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመዋል።
የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ ገደብ እንድጠናቀቁ አሁንም ያልተቋረጠ ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠይቀዋል።
በንጉሰ ወልደየስ
