


2017 ዓ.ም ይቻላል ተብለው ያልታሰቡ ጉዳዮች የተከናወኑበት እና የስኬት ዓመት ነበር፣
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የግብርና መር ፖሊሲ ይከተል ነበር ይህንን ወደ ብዝሀ ዘርፍ ቀይረን በእጅጉ ውጤታማ ሆነናል፣
በአንድ ሴክተር ላይ ተንተርሶ መስራት ከድህነት አረንቋ ስለማያወጣን ብዝሀ ዘርፍን በመከተላችን ውጤት አምጥተናል፣
ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ እነዚህ አምስት ግንባር ቀደም ሴክተሮች ብዝሀ ዘርፍ ሆነው ቢመሩ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ሊያሻሽሉ ይችላ የሚል እምነት ነበረን፣
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስር ነቀል ውጤት እንዲያመጣ ብዝሀ ዘርፍ መንግስት ከአጋር ድርጅቶች ጋር ተሳስሮ የኢትዮጵያ ዕድገት ለማፋጠን ይሰራል፣
መንግስት ከህዝብ ጋር ተሳስሮ የኢትዮጵያን ልማት በየፈርጁ ማፋጠን አለበት፤ በመንግስት ደረጃ ግልጽ አቅጣጫ የተቀመጠለት ከለውጡ በኋላ ነው፣
ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ እንቅስቃሴ ባለፉት ዓመታት 48 ቢሊየን ችግኞችን ተክላለች፤ ይህም በዓለም ላይ ትልቁ የደን ልማት ነው።
ይህንንም ለእያንዳንዱ ችግኝ 1 ዶላር ቢወጣ በጠቅላላው 48 ቢሊየን ዶላር ለአየር ንብረት ለውጥ ኢትዮጵያ ኢንቨስት አድርጋለች፣
የኢትዮጵያ መንግስት ይህን ያህል ገንዘብ ብቻውን ሊያሳካው አይችልም ነገር ግን ከ25 ሚሊየን በላይ የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን በየአመቱ ጊዜያቸውን ጉልበታቸውን ሳይታክቱ በመስራታቸው ያንን ሚያክል ሃብት ያስወጣ የነበረን ስራ በመንግስት እና በህዝብ ቅንጅት ማሳካት ተችሏል።
