



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ የለውጡ መንግስት ለንግድና ኢንቨስትመንት ዕድገት የፈጠረውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም የክልሉን ኢንቨስትመንት በመለየት፣ በማጥናት እና ልማታዊ ባለሀብቶችን በመደገፍ በዘርፉ ውጤታማ ተግባራትን ለማከናወን መቻሉን በመክፈቻ ንግግራቸው አንስተዋል።
በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመለየትና በማጥናት በዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ የሀገራችንን ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በክልሉ የሚመረቱ ምርቶችን በነፃ ገበያ መር አሰራር መሠረት የማቅረብ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰው በሩብ ዓመቱ ከ1ሺህ 5መቶ በላይ የሚሆኑ ህገወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ የንግድ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲገቡ መደረጉን አስረድተዋል።
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እየቀረበ ያለ ሲሆን ውይይት እንደሚደረግበትም ይጠበቃል።
በካሳሁን አሰፋ
