


የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ሲያካሂድ የነበረው የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተጠናቀቀ።
ኮሚሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት በፓርቲው ጉባኤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ዘርፍ ብዙ ተግባራት ማከናወኑን ነው የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ያዙ የገለጹት።
ለኮሚሽኑ ተግባር ውጤታማነት ማነቆ የሆኑ የአሰራር ችግሮችን በመለየት በቶሎ መፍታት እንደሚገባ የገለጹት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ በየደረጃው የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወጥነት ባለ መልኩ ኮሚሽኑን የመደገፍ ተግባሩን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የፓርቲውን አሰራር በመከታተል የሚታዩ ችግሮችን ፈጥኖ የማረም ተግባርን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ የፓርቲው እሳቤ በአባሉ ውስጥ መተከሉን እና ጠንካራ የውሰጠ ፓርቲ አሰራር መኖሩን የማረጋገጥ፤ከአባልና አመራር የሚቅርቡ አግብቢነት ያላቸው ቅሬታዎችን መፍትታ እንዲሁም በሂደቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን የማረም ተግባሩን ማጠናከር እንደሚገባም ነው አቶ ፀጋዬ ያስገነዘቡት።
በመድረኩ የዞንና ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽን አመራሮች የስድስት ወራት የአፈጻጸም ሪፓርት ያቀረቡ ስሆን ከሪፖርቱ መነሻ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በዕድገቱ በዛብህ
