የዩናይትድ ኪንግደም የግብርና ንግድ ልዑክ (UK Agribusiness Trade Mission) በኢትዮጵያ በግብርና የኢንቨስትመንት መስኮች የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።
የግብርና ሚኒስትር ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪ ጫላ ሆርዶፋ(ዶ/ር) ከልዑኩ ጋር በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።
በመድረኩ በወተት ሀብት፣ በዶሮ፣ በማር፣ በእንስሳት ጤና፣ በዘርና በእንስሳት መኖ ልማት የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ምክክር ተደርጓል።
ለልዑክ ቡድኑ በኢትዮጵያ ስላሉ የግብርናው የኢንቨስትመንት እድሎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በምግብ ሰብል፣ በቅባት ሰብል፣ በጥራጥሬ ሰብልና በኢንዱስትሪ ሰብሎች ከኢንቨስትመንት አማራጮቹ መካከል እንደሚገኙበት ተገልጿል።
በእንስሳት ሀብት ልማት፣ በግብርና ሜካናይዜሽን፣ በመስኖ ልማት፣ ለአፈር ለምነት የሚውል የኖራ ምርትና በተፈጥሮ ማዳበሪያ ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮችና የገበያ እድሎች እንዳሉ ተመላክቷል።
የግብርና ሚኒስትር ከፍተኛ የፖሊሲ አማካሪ ጫላ ሆርዶፋ(ዶ/ር) የግብርናው ዘርፍ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ፣ ለስራ ዕድል ፈጠራና ኢኮኖሚን በማሳደግ ትልቅ አበርክቶ እንዳለው ገልጸዋል።
መንግስት ለእንስሳት ሀብት ልማት በሰጠው ትኩረት ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝም አመልክተዋል።
የግብርና ዘርፉን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ የግሉ ዘርፍና ባለሀብቶች ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ያላት እምቅ የውሃ ሀብት ለግብርና ኢንቨስትመንት ትልቅ ዕድል እንደሆነ ገልጸው ባለሀብቶችም መንግስት ለግብርና ኢንቨስትመንት የሰጠውን ማበረታቻ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም የግብርና ንግድ ልዑክ ቡድን አባላት የቀረበላቸውን አማራጮች ተጠቅመው በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራትና ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
የዩናይትድ ኪንግደም የግብርና ንግድ ልዑክ በኢትዮጵያ በግብርና ኢንቨስትመንት መስኮች መሰማራት እንደሚፈልግ ገለጸ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2017(ኢዜአ):- የዩናይትድ ኪንግደም የግብርና ንግድ ልዑክ (UK Agribusiness Trade Mission) በኢትዮጵያ በግብርና የኢንቨስትመንት መስኮች የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።