የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በክልሉ የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ይገኛሉ



የ ከተማ አስተዳደሩ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) ሠራተኞችና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላተ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በፕሮግራሙ የተሰሩ ስራዎች የልምድ ልውውጥ የመስክ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው።
የጉብኝቱ ዓላማ በክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የተከናወኑ ውጤታማ አፈጻጸሞች ላይ የልምድ ልውውጥና የተሞክሮ ቅመራ ለማድረግ ያለመ ነው።
በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አማካሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ መላኩ ክልሉ አዲስና የለውጡ መንግስት የፈጣን ምላሽ ውጤት መሆኑን በመጥቀስ በግብርናው ዘርፍ በርካታ ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል ።
በክልሉ በግብርናው ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ከተለያዩ ፕሮግራሞች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
ከነዚህም አንዱና የአንበሳውን ድርሻ እየተጫወተ ያለው የስርዓተ ምግብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) መሆኑን በመግለጽ ፕሮግራሙ ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ዓይነተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አንስተዋል።
የእእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድወሰን ሁሴን ፕሮግራሙ በዘጠኝ ክልሎች እና ሁለት ከተማ አስተዳደር የሚከናወን መሆኑን ተናግረዋል ።
በክልሉ ውስጥ በ6 ዞኖች በ15 ወረዳዎች የሚሰራ መሆኑን በመጥቀስ በፕሮግራሙ በጀት ድጋፍ የተከናወኑ ተግባራት ማየትና ልምድ በመቅሰም ተሞክሮ ለማስፋት የድረዳዋ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ክልሉን መርጦ በመምጣታቸው አመስግነዋል።
በመሆኑም በክልሉ ቆይታ አስፈላጊ ሁሉ እንደሚደረግላቸው አንስተዋል ።
ጉብኝቱ በፕሮግራሙ የተገነባ በካፋ ዞን ጨና ወረዳ የጎታ ቀናች የተቀናጀ የዓሣ እርባታ በመጎብኘት ተጀምሯል ።
በጌታሁን ግርማ
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
