በህዳሴ ግድብ የሚሰማሩ የባህር ዳርቻዎች ጥበቃ የፖሊስ ምልምል አባሎች ተመረቁ

Spread the love

በህዳሴ ግድብ የሚሰማሩ የባህር ዳርቻዎች ጥበቃ የፖሊስ ምልምል አባሎች ተመረቁ

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚሰማሩ የባህር ዳርቻዎች ጥበቃ የፖሊስ ምልምል አባሎችን በመሰረታዊ ባህርተኝነት አሰልጥኖ አስመርቋል።

በባቦጋያ ማሪታይም እና ሎጂስቲክስ አካዳሚ በተካሄደው የምረቃ መርሐ ግብር የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እንዳሉት፤ ስልጠናው በዓለም አቀፍ መስፈርቶች መሰረት የተከናወነ ነው።

የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ዳግማዊ ዓድዋ ነው በማለት ገልጸው፤ የፌዴራል ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ግድቡን ከጅማሮው አንስቶ ሲጠብቁ ቆይተዋል ብለዋል።

በለውጡ መንግስት አማካኝነት ግድቡን ከነበረበት ውድቀት በማዳን ለስኬት ማብቃት መቻሉን ገልጸዋል።

የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ሀገር እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እና በአካዳሚው በኩል ባህርተኞችን ለዓለም ገበያ እያበቃ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በሁሉም መስክ እያንሰራራች ያለችውን ኢትዮጵያ ወደኋላ የሚመልሳት ኃይል እንደሌለ ተናግረዋል።

የባቦጋያ ማሪታይም እና ሎጂስቲክስ አካዳሚ ዲን ሲራጅ አብዱላሂ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው ስልጠናው ዘመኑን የዋጀ ዓለም አቀፍ ይዘቱን የጠበቀ እንደሆነ ገልጸው፤ ሰልጣኞች አስፈላጊውን እውቀትና ባህሪ ታጥቀዋል ብለዋል።

በመርሀ ግብሩ ለስልጠናው መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ እና በስልጠናው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ እውቅና መሰጠቱንም ኢዜአ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *