የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 43ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 43ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በዚህም መሠረት፦

1ኛ.የተለያዩ የቀረቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቷል።በዚህም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን 11 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን 10 በግብርና ዘርፍ እና 1 በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመሰማራት 500 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል መጠን በማስመዝገብ የቀረቡ ኢንቨስትመንት ጥያቄዎችን መርምሮ ወደ ስራ እንዲገቡ ወስኗል።

2ኛ. መስተዳድሩ ምክር ቤቱ በሁለተኛ አጀንዳነት የተወያየዉ የደቡብ ምዕራብ ማዕድን ኮርፖሬሽን ለማቋቋም የቀረበዉን ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *