በዞኑ ሰፊው ወጣቶችን የሚያቅፍ የገጠር የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ኮንታ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት ሰፊ ወጣቶችን የሚያቅፍ የገጠር፣ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ገለጸዋል።

በዞኑ፣ አመያ ዙሪያ ወረዳ፣ በጊምባ አጋሬ ቀበሌ በቡና ልማት ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ወጣቶች በበኩላቸው በዘርፉ ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዞኑ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራን በመሠረታዊነት በመደገፍ ዘርፉን ለማሻገር ትኩረት መሰጠቱን የገለጹት አስተዳዳሪው፥ በዚህም በዞኑ ያለውን እምቅ የግብርና አቅም በተሟላ መልኩ ጥቅም ላይ ለማዋልና በሂዴቱም ለዜጎች ሥራ ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ በዞኑ ሶስት መዋቅሮች በቁጥር ስምንት እያንዳንዳቸው 200 ወጣቶችን የሚያቅፉ የእርሻ ማዕከላት የማደራጀት ሥራ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ በማንሳት፣የመሬት ዝግጅት፣ ቀላልና አነስተኛ የማምረቻ ማሽነሪዎች ግዢ የማሳለጥ ተግባር እየተከናወነ ነው ያሉት አቶ ታከለ ተስፉ፥ ለተግባሩ የዞኑ መንግሥት ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል።

የቡና ልማት ኢንዱስትሪ ሰብሳቢ ወጣት አንድነት ታደለ እንደገለፀው ማኅበሩ 10 አባላትን በመያዝ በአነስተኛ ካፒታል የተቋቋመስሆን አሁን ላይ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ቋሚ ሀብት ማፍራት መቻሉን ገልጸዋል።

በዘንድሮው የምርት ዘመን 200 ኩንታል ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ሰፊ የዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን የገለጸው ወጣት አንድነት በሂዴቱም ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።

የመንግሥት ድጋፍና ክትትል ለተሻለ ውጤት እንዳደረሳቸው የገለጸው ሌላኛው የማኅበሩ አባል፥ አለማየሁ አሰፋ አሁን ላይ በቡና ልማት ሥራ ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የቀበሌው የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀበሻው ዶላንጎ በበኩላቸው፥ ወጣቶቹ የሥራ ባህልን በማሻሻልና ውጤታማ በመኾን ለሌሎች ምሳሌ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *