ከገጠር ትራንስፎርሜሽን ወደ ኢንዱስትራላይዜሽን ለሚደረገው ሽግግር የመንግስትና ግል ባንኮች ትብብርና ድጋፍ አጋዥ ነው፦አቶ ማስረሻ በላቸው

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የኢንዱስትሪ እና ኢኖቬሽን ቢሮ ከግልና መንግስት ባንኮች ጋር በመቀናጀት የኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጤታማ ማድረግ በሚያስችል ጉዳዮች ዙሪያ በቦንጋ ከተማ እየተወያየ ነው።

በውይይቱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፤ በክልሉ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል የመንግስት እና የግል ባንኮችን ያሳተፈ ካውንስል መቋቋሙን ተናግረዋል።

የገጠር ትራንስፎርሜሽን እውን በማድረግ ወደ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር በሚደረገው እርምጃ የሁሉም ዘርፍ ትብብርና ድጋፍ አስፈላጊ ነው ያሉት አቶ ማስረሻ ከእነዚህ ብዝሀ ዘርፎች መካከል የመንግሥት እና ግል ባንኮች ሚና ዋነኛ ነው።

የመንግስት እና ግል ባንኮች የፋይናንስ ብድር እና ግብዓት በማቅረብ እንዲሁም ጥናትና ምርምር ብሎም አሰሳ እና ዳሳሳዎችን በማካሄድ ረገድ ሚናቸው ከፍተኛ ነውም ብለዋል ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ።

ያለባንኮች ድጋፍና ተሳትፎ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍን ውጤታማ ማድረግ አይቻልም ያሉት አቶ ማስረሻ ፤ ከገጠር ትራንስፎርሜሽን ወደ ኢንዱስትራላይዜሽን ለሚደረገው ሽግግር የመንግስትና ግል ባንኮች ትብብርና ድጋፍ አጋዥ እንደሆነም ገልጸዋል።

ክልሉ ከሚያመነጨው ሀብት እንዲሁም የመንግስት እና ግል ባንኮች በግል፣ በማህበር ለሚንቀሳቀሱ ማህበራት እና ኢንቨስተሮች የፋይናንስ እና የግብዓት አቅርቦት በማመቻቸት የዘርፉን ጉዞ እውን እንዲያደርጉ መሥራት እንደሚጠበቅ ነው አቶ ማስረሻ በላቸው የገለጹት ።

ከተለያዩ ዘርፎች በጋራ ትብብርና ቅንጅት የኢንዱስትሪ ዘርፍን ውጤታማ ለማድረግ በሚደረገው እርምጃ በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ለዘርፉ የሚያደርገውን እገዛና ድጋፍ እንደሚያጠናክርም አረጋግጠዋል።

በክልሉ የኢንዱስትሪ እና ኢኖቬሽን ቢሮ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ዘመድኩን ሰለሞን ለመወያያ የተዘጋጀውን ሰነድ እያቀረቡ የሚገኙ ሲሆን ከሚቀርበው ሰነድ መነሻ የጋራ ውይይት ይደረጋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *