በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ያሉትን የመልካም አስተዳድር ችግሮችን ለመቅረፍ በቦንጋ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው።

Spread the love

‎የ2017 የከተማ ልማት ስራዎች የፈጻሚና አስፈጻሚዎች የአፈጻጸም ሂደት በጥንካሬና በጉድለት በሚያሳይ ግምገማዎች እና በቀጣይ የማስፈጸሚያ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው።

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ልዩ ረዳት አቶ አለማየሁ አይበራ በመድረኩ እንደገለጹት በብልጽግና ፓርቲ የሚመራ መንግስት ለከተሞች ልማት ከምንጊዜውም በላይ በፖሊሲም ሆነ በተግባር ትኩረት ሰጥቶ እየተገበረ ይገኛል ብለዋል።

‎ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ በማድረግ የተሰሩት የኮርደር ልማት ስራዎች ከተሞቻችን አረንጓዴ፣ ውብ ንጽህ እና ሳቢ እንዲሆኑ እድል የከፈተ በመሆኑ ልዩ ትኩረት በመስጠት የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደመገባ ጠቅሰዋል።

‎የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢር ኃላፊ ኢ/ር የማታለም ቸኮል እንደገለጹት ባለፋት ዓመታት በዘርፉ የሚመሩ ሥራዎችን በኃላፊነት ለመፈጸም የተደረጉ አበረታች ጥረቶች ቢኖሩም አሁንም ቢሆን በሙሉ አቅም በኃላፊነትና በተጠያቂነት ስሜት ከመፈጸም እና ከማስፈጸም ረገድ ሰፊ ጉድለት መኖሩን አንስተዋል።

‎ በየጊዜዉ ህዝቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት መንግስት የተለያዩ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ብርቱ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *