የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የሥራ ጉብኝት ክልሉ አርሶና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነትን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ የተለያዩ ኢኒሼቲቦች ፍጥነትና ጥራትን ማዕከል ባደረገ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል።

Spread the love

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በምዕራብ ኦሞ ዞን መኒኢት ጎልዲያ ወረዳ ጫት ቀበሌ እየተገነባ ያለውን ሞዴል የገጠር መንደር ጎብኝተዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት የተጀመረው የሞዴል ገጠር መንደመር በክልሉ በፍጥነትና ጥራትን ማዕከል ባደረገ መልኩ እየተከናወነ ነው።

ሞዴል የገጠር መንደር የሰውና የእንስሳትን ቤት ከመለየት አንስቶ ለመኖሪያ ቤት ምቹ ሁኔታዎችን በማሟላቴ የገጠሩ ማህበረሰብ ጤናቸውን እንዲጠብቁና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በተመሳሳይ በጀሙ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን አዳሪ.ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሌላኛው የጉብኝቱ አካል ነበረ።

በተመሳሳይም በቤንች ሸኮ ሲዝ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የሲዝ ኮንስትራክሽን እና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ያለበት የግንባታ ያለበት ሂደት ጉብኝት ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *