ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሲቆሙ የማያሳኩት ነገር እንደሌለ ህያው ምስክር ነው

Spread the love

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሲቆሙ የማያሳኩት ነገር እንደሌለ ህያው ምስክር ነው – የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሲቆሙ የማያሳኩት ነገር እንደሌለ ህያው ምስክር መሆኑን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በህብረት እውን የሆነ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን አብሳሪ እና የዘመናት ህልምን የማሳካት አብነት ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ በብዙ ልፋትና መስዋዕትነት የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በቅርቡ እንደሚመረቅ ማብሰራቸው ይታወሳል፡፡

ኢዜአ የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅን አስመልክቶ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዚህ ዘመን ትውልድና የመንግሥት ቁርጠኝነት ያሳካው ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ እንዳሉት፤ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በጋራ እውን ያደረጉት ዳግማዊ ዓድዋ ነው፡፡

ግድቡ ኢትዮጵያውያን በትብብር እውን ያደረጉት ትውልድ ተሻጋሪ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን አንስተው በተባበሩ ብርቱ እጆች ሀገራዊ ግብን ማሳካት እንደሚቻል ያስመሰከረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን አቅማቸውን በማስተባበር ደጋግመው አኩሪ ታሪክ መስራት እንደሚችሉ በዚህ ብሔራዊ የልማት አርበኝነት በተገለጸበት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ማሳየታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ(ኢዜማ) የሐረሪና የድሬዳዋ የዞን ምክር ቤት ሰብሳቢ ዮናስ በትሩ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተባበረ ክንድ እውን የሆነ የሀገር የኢኮኖሚ ዋልታ ነው ብለዋል፡፡

ግድቡ ኢትዮጵያውያንን ያስተሳሰረ ትውልድ ተሻጋሪ ብርሃን መሆኑን ጠቁመው ስለመተባበር ኃይል ለትውልዱና ለአፍሪካውያን ትምህርት መስጠቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያውያን በአንድነት ከቆሙ የማያሳኩት ነገር እንደሌለ ግድቡ ህያው ምስክር መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የወለኔ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ፈይሰል አብድላዚዝ በበኩላቸው ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያን እመርታ፣ አንድነት እና በጎ ገጽታ በተግባር ያሳየ ብሔራዊ የኩራት ምንጭ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሀገርን ኢኮኖሚ ከማሳደግ አኳያ ግድቡ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመው በህዝብ ትብብርና ተሳትፎ የተገነባ የህብረት መገለጫ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *