ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ የተቋማት ግንባታን ማጠናከር ይገባል
“ወደ ተምሳሌት አገር በተሻገር ሕልም፤ በላቀ ትጋት አስተማማኝ ስራ መስራት” በሚል መሪ ቃል ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና መድረክ ተጠናቋል፡፡



የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የጽ/ቤቱ ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ እንደገለጹት ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ የተቋማት ግንባታ ማጠናከር ይገባል፡፡
በሁሉም ተቋማት የአገልግሎት ልህቀት ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ መስራት እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡
ብሔራዊ ጥቅም ለማሳካት ከሌሎች አካላት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ሚዛናዊ እይታና ተራማጅ መሆን እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
አካታች ተቋማትን በመገንባትና ሲቪል የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከር የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በባለቤትነት መንፈስ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የውስጠ ፓርቲ አንድነት፣ ጥንካሬና ጥራት ማረጋገጥ ከፋፋይና ሰርጎገብ አጀንዳዎች መታገል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
አመራሩ የብልጽግና እሴቶችን በመላበስ ለሕዝብ የገባናቸው ቃሎች በተግባር በመፈጸም ውጤታማነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል፡፡
አስተሳሳሪና ገዥ ትርክትን በመጠቀም በየተቋሙ ያሉ ውስጣዊ ችግሮች በመፈተሽና በእቅድ በመምራት ሃላፊነትን በአርአያነት መወጣት እንደሚገባም በማብራሪያቸው አሳስበዋል፡፡
