የአካባቢ ገበያዎች ደረጃቸውን ወደ ጠበቁ የገበያ ማዕከላት የማሻገር ተግባር ይከናወናል – ሚኒስቴሩ

Spread the love

የአካባቢ ገበያዎች ደረጃቸውን ወደ ጠበቁ የገበያ ማዕከላት የማሻገር ተግባር ይከናወናል – ሚኒስቴሩ

የአካባቢ ገበያዎች ደረጃቸውን ወደ ጠበቁ የገበያ ማዕከላት የማሻገር ተግባር እንደሚከናወን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስቴሩ “በተሳለጠ ንግድ ወደ ሚጨበጥ ሀገራዊ ተስፋ” በሚል መሪ ሃሳብ ሀገራዊ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር የዘርፍ ጉባዔ ተካሂዷል።

በጉባዔው የገበያ ማዕከላትን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) የማጠቃለያ ሀሳብ በሰጡበት ወቅት፤ በየአካባቢው ደረጃቸውን የጠበቁ የገበያ ማዕከላትን በመገንባት አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ ማገናኘት ይገባል ብለዋል።

የገበያ ማዕከላቱ ደረጃቸውን ጠብቀው ለኅብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ እያስቻሉ መሆኑን አንስተው፤ በአዲስ አበባ አስተዳደር፣ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ሌሎች ክልሎችም ይህን ተሞክሮ በመውሰድ ወደ ተግባር መግባት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ሚኒስቴሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ መስፈርትና ዲዛይን የማዘጋጀት ሥራዎችን እንደሚያጠናቅቅም ጠቅስዋል።

በዚህ ሂደት ማህበረሰቡን በንቃት ማሳተፍ እንደሚገባም ነው ሚኒስትሩ ያመላከቱት።

አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ ለማገናኘትና የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት አስተዋጽኦ ያላቸው የቅዳሜና እሁድ የግብይት ማዕከላት ቀደም ሲል ከነበረበት 1ሺህ 066 በ2017 በጀት ዓመት አዳዲስ ገበያዎችን በመክፈት 1,567 መድረሱ መገለጹ ይታወሳል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *