ከዘንድሮው የመኸር ወቀት ከ672 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል – ሚኒስቴሩ

በዘንድሮው 2017/18 የመኸር ወቅት ከ672 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
በስንዴ ዘር ሦስት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ሔክታሩ መሸፈኑም ተገልጿል።
በግብርና ሚኒስቴር የሰብል ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ኢሳያስ ለማ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ እንደ ሀገር እስካሁን 19 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ታርሷል።
በአጠቃላይ በመኸር እርሻ በአነስተኛ አርሶ አደሮችና በባለሃብቶች ከሚታረሰው መሬት 672 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል ነው ያሉት።
በአሁኑ ወቅት ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው ከሆኑ አካባቢዎች በስተቀር በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍል ዘር መዝራት ተጠናቋል።
በሀገር ደረጃ ምርታማነትን የማሳደግ ስራ ትኩረት እንደተሰጠው ጠቁመው፤ ክልሎችም የግብዓት አቅርቦት ላይ የተጠናከረ ስራ እንዲሰሩ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁን ወቅት ባለው የአየር ትንበያ መሰረት በመኸር አብቃይ አካባቢዎች የሚጠበቀው መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ በዘርፉ የታቀዱትን ተግባራት ማሳካት የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
በዘር በተሸፈኑ ማሳዎች የሰብል እንክብካቤ በስፋት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በሰብል ላይ በሽታ እንዳይከሰት አርሶ አደሩ የተሻሉ ዝርያዎችን እንዲጠቀምና የአረም ስራዎች ላይ ትኩረት እንዲያደርግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በስንዴ ዘር ከተሸፈነው ሦስት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ሔክታር መሬት ውስጥ ሁለት ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሔክታሩ በክላስተር የታረሰ መሆኑን አብራርተዋል።
በአጠቃላይም በመኸር እርሻ 176 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቅሰዋል።
በስንዴ ምርታማነት በተሰሩ ስራዎች ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ምርቱን ከውጭ ማስገባት ማቆሟን ጠቅሰው፤ ለተገኘው ስኬት በተለይ የክላስተር እርሻና የመስኖ ስንዴ ልማት ስራ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
በሊንክደን
