በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተማሪዎች ምዝገባ ከፊታችን ነሃሴ 19/2017 ዓ. ም በይፋ ይጀመራል

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የተማሪዎች ምዝገባ ከፊታችን ነሃሴ 19/2017 ዓ. ም በይፋ ይጀመራል።

የተማሪዎች ምዝገባ በወቅቱ ማካሄድ የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር እንደሚያግዝ ተገልጿል።

የ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ስራውን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ለማስጀመር በክልሉ ባሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የፊታችን ሰኞ በቀን 19 የተማሪዎች ምዝገባ እንደሚጀመር የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ ለክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በሰጡት መግለጫ የ2018 ዓ/ም የመማር ማስተማር ስራን በወቅቱ ለማስመጀመር የተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 19/2017 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚከናወን ተናግረዋል ።

በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ እንደሚጀመር የገለጹት የትምህርት ቢሮ ኃላፊው መምህራንና የትምህርት ቤት ባለድርሻ አካላት በየትምህርት ቤታቸው በመገኘት የተማሪዎችን ምዝገባ እንዲያከናዉኑ አሳስበዋል ።

የተማሪዎች ወላጆች ከነሐሴ 19/2017 ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ አንድም ተማሪ ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይቀር ማስመዝገብ እንዳለባቸውም አቶ አልማው በመግለጫቸው ገልጸዋል።

በክልላሉ በሁሉም ዞኖች ከነሃሴ 19 ጀምሮ በተደራጀ መልኩ የተማሪ ምዝገባ በማካሄድ 965284 ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት ልዩ ርብርብ እንደሚደረግ ኃላፊዉ ጠቅሰዋል።

የተማሪዎች ምዝገባ በወቅቱ መከናወኑ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ወሳኝ በመሆኑ ለዚሁ ስኬት ተማሪዎችን በወቅቱ ማስመዝገብ ይገባል ሲሉም አቶ አልማው ጥሪ አቅርበዋል ።

በታጠቅ አበበ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *