ግብርን በታማኝነት በመክፈል ሀገር ወዳድነታችንን እንግለፅ!

Spread the love

እየጨመረ የመጣው የክልላችን የመልማት ፍላጎት እውን የሚሆነው ባለን ታማኝ የግብር ከፋዮች ቁርጠኝነት ብቻ ነው።

በማይጎረብጡ መንገዶች ለመጓዝ፣የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለመሆን፣ በት/ት እና በጤና ተቋማት የተሟላ አገልግሎት ለማግኘት ግብርን በታማኝነት መክፈል ቀዳሚና ትንሹ ግዴታችን ነው።

በ2016 የበጀት ዘመን 6.6 ቢሊዮን ብር ከተለያዩ የገቢ መሰረቶች ለመሰብሰብ ግብ ጥሎ እየተንቀሳቀሰ ካለው የክልላችን መንግስት ጎን ለመቆም ወቅቱ አሁን ነው።

ሰላሙ የተጠበቀለት ኢትዮጵዊ የዛሬን ብቻ የማያይ የሃገሩን ዕድገት ከሩቅ የሚያልም እየዘመነ በሚመጣው አሁናዊ አለም ተወዳዳሪ የንግድ ስርኣት ተጋሪ ለመሆን ያሰበ ግብሩን በታማኝነት የመክፈል ግዴታውን በውል የተገነዘበ ጀግና ዜጋ ነው።

ከግብር ስወራ፣ ከሃሰተኛ ሰነዶች ራሱን ያገለለ ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ የተለዩ የገቢ መሰረቶች ተፈፃሚ እንዲሆኑ የሚተጉ እጆችን በብርቱ የሚደግፍ የገቢ ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ ነው ብሎ የሚያምን እርሱ የተግባር ሰው ነው።

እርስዎ ግብርዎን በወቅቱና በታማኝነት ከፍለዋልን?
እንግዲያውስ ጥያቄው ለእርስዎ ነው!

ግብርን በወቅቱ በመክፈል ለሀገር ከብር መቆምዎን በተግባር ያሣዩ።

   ግብር ለሃገር ክብር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *