


የክልሉ የመንግስት የስድስት ወራት አፈፃፀም ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በተገኙበት በቦንጋ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል።
በመድረኩ የክልሉን ዋና ዋና የመንግስት አፈፃፀም የስድስት ወር ሪፖርት ያቀረቡት የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ የፍትህ ዘርፉን ማዘመንና ተደራሺነትን ማስፋፋት በመንግሥት በልዩ ትኩረት ከሚፈፀሙ ተግባራት አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።
ነፃና ገልለተኛ የፍትህ ተቋማትን ለመገንባት የተወሰደው እርምጃ ውጤት እያስመዘገ መሆኑን በኮንትሮባንድ እና በህገ ወጥ ተግባራት የፈጸሙ 123 ግለሰቦች ላይ ህግ የማስከበር ሥራ መሰራቱን ጠቁመዋል።
የፍትህ ተደራሽነትን ለማስፋፋት ባህላዊ ፎርድ ቤቶችን ማቋቋምና ማጠናከር ትኩረት መደረጉን ገልፀው በበጀት ዓመቱ በ605 ቀበሌዎች ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ተቋቁመው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና ለማዘመን ዓላማን ይዞ በተደራጀው የአንድ ማዕከል አገልግሎት እስከአሁን ከ6500 በል ተገልጋዮች አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልፀው አገልግሎትን ለማስፋፋት በሁሉም ዞን ከተሞች ማዕከሉን ለመገንባት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ዘላቂ ለማድረግ የማህበረሰብ ተኮር ዉይይቶችም ተጠናክረዉ መቀጠላቸዉንና የክልሉ የጸጥታ አቅምም የማጠናከር ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።
የመንግስት አገልግሎትን ለማዘመን በተሰራዉ ሥራ በሚዛን አማን ከተማ ተገንብቶ ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን በሌሎች ከተሞች ይህንን ለማስፋት ቅድመ ዘግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸዉ ተመላክቷል
በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ በራስ አቅወምና።ሚዲያዎችን በማስተባበር እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።
ሀሰተኛ መረጃና የተሳሳተ ትርክት በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ልፈጥር የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖዎችን በመገንዘብ ሁሉም በጋራ ልያውግዝ ይገባል ብለዋል።
በንጉሰ ወልደየስ
