







የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በቦንጋና ታርጫ የሳተላይት ደም ባንኮች ደም ለማሰባሰብና ለማሰራጨት 3 ሺህ 450 ዩኒት ለማሰባሰብ ታቅዶ 82 በመቶ መፈፀም መቻሉንና በወባ በሽታ የመያዝ ምጣኔን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር በ29.5 መቀነስ መቻሉም በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህንም የአገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል በአጠቃላይ እስከ 6 ወር 325 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን ኃላፊዋ ገልጸዋል።
በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች 37 ሺህ 912 እናቶች የወሊድ አገልግሎት ያገኙ ሲሆን በግማሽ ዓመቱ ውስጥ ከታቀደዉ 54 ሺህ 104 እናቶች አንጻር 70% ለመፈጻም ተችሏል።
በትምህርት ዘመኑ ትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ሀብት አሰባሰብ በግማሽ ዓመት 3መቶ 92 ሚለዮን ብር ተሰብስቧል።
60 ሞዴል ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን ከእነዚህ ዉስጥ 27 የመማር ማስተማር ስራ መጀመራቸዉም ተመላክቷል።
የሴቶች መብትና ሁለንተናዊ ደህንነት ለማስጠበቅ 37ሺህ 9መቶ ሴቶችን ለማደራጀት ታቅዶ 34ሺህ 265 በመፈጸም 90 በመቶ መከናወኑ ተጠቅሷል።
የወጣቶችን ተሳትፎና ውክልና ለማሳደግ በክረምትና በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ14የስምሪት መስኮች 682ሺህ ለማሳተፍ ታቅዶ 97በመቶ መከናወኑ ተገልጿል።
ባለፉት ስድስት ወራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በማህበራዊ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸው ተገልጿል።
በካሳሁን አሰፋ
