“ቲካሻ ቤንጊ ” ባህላዊ ይዘቱና ስርዓቱን ተጠብቆ በድምቀት ለማክበር በትኩረት እየተሰራ ነው ።

Spread the love

የሸኮ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ” ቲካሻ ቤንጊ” በመጪው ወርሃ ጥር እንደሚከበር ተጠቁሟል ።

የሸኮ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ” ቲካሻ ቤንጊ” በመጪው ወርሃ ጥር እንደሚከበር ተገለጸ።

የሸኮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሪ ጉርሙ እንደገለጹት በዓሉ አሮጌው ዓመት የሚሸኝበት አዲሱ አመት በተስፋ የምንቀበልበት መሆኑን በመግለፅ ዘንድሮ ከወትሮ በተለየ ከፍ ብሎ ለማክበር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ባህላችንን የምናስተዋውቅበት በመሆኑ ባህላዊ ይዘቱ እና ስርዓቱ ተጠብቆ ለማክበር ከአብይ ከሚቴ ስር የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎች ተቋቁመው ወደስራ መግባታቸውን ገልጸዋል።

የብሄረሰቡ አባላት በባህላዊ አልባሳቶቻቸው ደምቀውና ተውበው የሚታዩበት፣በባህላዊ ጭፈራቸው የሚደምቁበት፣የተለያዩ በህላዊ ክዋኔዎች የሚስተናገዱበት፣ ከበኩር እህል በአይነት በአይነቱ ማዕድ በጋራ የሚጋሩበት የመተሳሰብ እሴቶች የሚጎለብቱበት ማህበራዊ ትሩፋት መሆኑን አመልክተዋል ።

የሸኮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታምራት ምናሴ በበኩላቸው የዘንድሮ የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ “ቲካሻ ቤንጌ” በልዩ ድምቀትና ድባብ ይከበራል ብለዋል ።

ምርት ተሰብስቦ ከጎተራው በመግባቱ፣አካባቢውም ከርሃብ፣ከበሽታ፣ከቸነፈር እንዲሁም ከተፈጥሮ አደጋ ተጠብቆ ለአዲሱ ዓመት በመድረሱ የብሄረሰቡ አባላት ለፈጣሪያቸው ስለተደረገላቸው መልካም ነገሮች ሁሉ ምስጋናቸውን በባህላዊ ስርዓቶቻቸው የሚያቀርቡበት ታላቅ በዓል መሆኑንም ከንቲባው አክለዋል።

“ቲካሻ ቤንጊ” ጥር 14 በቀበሌዎች ፣ጥር 15 በፓናል ውይይት እንዲሁም ጥር 16 ዋናው በዓል በሸኮ ከተማ በድምቀት እንደሚከበር መገለጹን የዘገበዉ የወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *