




ዛሬ የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ።
ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊ እና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው። በውይይታችን የሁለትዮሽ ግንኚኙነታችንን በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ የተለዋወጥን ሲሆን ይኽም በሰላም እና መረጋጋት፣ ንግግር ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር።
