የመስኖ ልማት የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመከላከል የጎላ ሚና እንዳለው ተጠቆመ

Spread the love

የመስኖ ልማት የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባሻገር የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመከላከል የጎላ ሚና እንዳለው የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አማካሪ ታየ ሙሉጌታ ኢትዮጵያ ያላትን ውሃዎች በመስኖ ተጠቅማ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል፡፡

በዚሁም ያላትን የውሃ ሀብት እና ሰፊ መሬት ተጠቅማ በመስኖ የምትለማ ሀገር መሆኗን አረጋግጣለችም ነው ያሉት።

ከጊዜ ወደ ጊዜ በመስኖ ልማት ከፍተኛ ወጤት እየተመዘገበ መምጣቱን ገልጸው፤ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖማ ለማሳደግ እንደሚረዳም አንስተዋል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *