የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የ2016 ሴክቶሪያል ጉባኤ እያካሄደ ነው

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የ2016 ሴክቶሪያል ጉባኤ እያካሄደ ነው

ቢሮው በ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት የአፈፃፀም ሪፓርትና በቀጣይ አቅጣጫዎች እንዲሁም ለተለያዩ የፋይናንስ የህግ ማዕቀፎች ዝግጅት ግብዓት ማሰባሰብ ላይ ያተኮረ ሴክቶሪያል ጉባዔ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባዔው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ ክልሉ ሲንከባለል የመጣውን የፋይናንስ ጉድለት ትርጉም ባለው መንገድ የማሻሻል አመርቂ ስራ በበጀት ዓመቱ ማከናወኑን ገልፀው የተገኘውን ውስን ሀብት በክልሉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲውል በማስቻል ረገድ በግልፅና አሳታፊ የአሰራር ስርዓት የተመራ እንደነበር አብራርተዋል።

የፋይናንስ አቅርቦትንም ለድህነት ቀናሽ ሴክተሮችና ለሰብዓዊ አገልግሎቶች የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠትና ወጭ ቆጣቢና ኢኮኖሚያዊ እንዲሆን የማድረግ ስራ መከናወኑም ኃላፊዋ ገልፀዋል።

ከጥር 21-23/2016 ዓ.ም በሚቆየው ጉባዔ በ6 ወራት የአፈፃፀም ሪፓርትና በፋይናንስ የህግ ማዕቀፎች ላይ ውይይት የሚደረግ ሲሆን በጉባዔው ላይ የክልል አመራሮች፥ የክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት፥ የ6ቱ ዞኖች የወረዳና የከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ኃላፊዎች ይሳተፋሉ።

በእንዳለማው ጌታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *