በክልሉ ለሚሰራው የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ሚና ወሳኝ እንደሆነ ተገለጸ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የ2017 ዓ/ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት የተግባር አፈፃፀም ግምገማ በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት በክልል ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ወንድወሰን ሁሰን የመድረኩ ዓላማ በ2017 በጀት ዓመት ሁለተኛ ሩብ ዓመት የተግባር አፈፃፀም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ጉድለት የታየባቸውን ጉዳዮች ከወዲሁ ለማረም እንደሆነ እንዲሁም በመስክ ጉብኝት ተሞክሮ ለመቀመርና የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ በጋራ ለማቀድ በማቀድ የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል ።

ፕሮግራሙ በክልሉ በ2015 ዓ/ም የጀመረና በስድስቱ ዞኖችና 15 ወረዳዎች 368 ቀበሌዎች 1.5 ሚለየን ህዝብን ተደራሽ ያደረገ መሆኑን አቶ ወንድወሰን ገልጸዋል ።

በመሆኑም ፕሮግራሙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅና የማስረጽ፣ ለአርሶ አደሮች ግብዓት ማቅረብ ጠንካራ የምግብ ስርዓት ለመገንባትና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ በሁሉም ዘርፍ የኤክስቴንሽን ድጋፍ ማድረግ፣ የመስኖ መሠረተ ልማት ዝርጋታና አጠቃቀም በማሻሻል ፣ የገበያ መሠረተ ልማት ለማሻሻል የግብይት ማዕከላትን በመገንባትና ገበያ ትስስር በማሻሻል እንዲሁም በክትትል ድፍና ግምገማ የገበያ ስርዓት በማጠናከር ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ስራ አስኪያጁ አንስተዋል።

ከነዚህም በመነሳት ፕሮግራሙ በሚያቅፋቸው ዞኖችና ወረዳዎች ባለፉት ጊዜያት 5 የመስኖ ተቋማት፣ 7 የግብይት ማዕከላት፣ 2 አነስተኛ ድልድዮች፣ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆን ተጨማሪ መጋዘንና የማር ማቀነባበሪያ እየተጠናቀቀ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ፕሮግራሙ ከዓለም ባንክ በተገኘው የበጀት ድጋፍ በመንግስት ተቋማት የሚመራና የሚከናወን በመሆኑ ለበለጠ የህብረተሰብ ተጠቃሚነት በየደረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን በአጽንኦት አክሏል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ቢሮ የምግብ ስርዓት ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ወንደወሰን ሁሰንን ጨምሮ የፕሮግራሙ ማኔጅመንት አባላት፣ የዞን ፎካል፣ ወረዳ የመጡ የፕሮግራሙ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች የባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *