የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ችቦ ንቅናቄ መድረክ ከግንቦት 02 – 03 /2016 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ተገለጸ\::

Spread the love

በክልሉ የፖለቲካና አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ቦንጋ ከተማ ላይ የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ችቦ አቀባበልና አሸኛኘት በዓል እንደሚደረግ ተገለፀ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የፖለቲካና አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ቦንጋ ከተማ ላይ የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ችቦ አቀባበል በዓል በደማቅ ሁኔታ እንደሚደረግ የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ተናግረዋል።

የቢሮው ኃላፊ በሰጡት መግለጫ መርሀግብሩ በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስተባባሪነት እንደሚሰራና

በመላው ሀገራችን የሚፈፀም እንደሆነ ተናግረዋል።

የኛም ክልል በአማራ ክልል ደሴ ከተማ ላይ በተደረገው ፕሮግራም ችቦውን እንደተቀበለ ገልፀዋል።

ቦንጋ ላይ የሚካሄደው የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ችቦ አቀባበልና የሽኝት መርሃ-ግብር ከካፋ ዞን አስተዳደርና ከዞኑ ባህል ቱሪዝም ስፖርት መምሪያ ጋር በመቀናጀት ከግንቦት 02 – 03 2016 ዓ.ም ድረስ በደማቅ ሁኔታ የሚካሄድ ሲሆን ይህም በአዳራሽ ውስጥ ፓናል ውይይትና በአደባባይ ላይ በተለያዩ ትርኢቶች የሚከበር በዓል መሆኑን ማብራራታቸዉን የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *