የሚዛን አማን ከተማ የኮሪደር ልማት ሥራ ተጎበኘ

Spread the love

የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ሃላፊና የከተሞች መሬት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ በሚዛን አማን የኮሪደር ልማትና ልዩ ልዩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ።

በከተማዋ በመንግስትና ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ ታክሎበት እየተገነባ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ የመጀመሪያ ዙር በተያዘለት የጊዜ ገደብ እየሄደና በጥሩ አፈጻጸም ላይ የሚገኝ መሆኑንም በምልከታ ወቅት ተገልጿል።

በመልሶ ማልማት ዘርፍ ከተማ አስተዳደሩ በወሰደው ቁርጠኝነት የግል ባለሃብቱ ወደ ግንባታ ከገባ ከገባ ቆየት ያለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በዘርፉ ግንባታቸውን አጠናቀው ለአገልግሎት ያዋሉና በመገንባት ላይ ያሉ መኖራቸውም የተጠቀሰ ሲሆን የሚገነቡት ግንባታዎች የከተማዋን ደረጃ ከፍ የሚያደርጉ መሆናቸው ተጠቅሷል።

በመሰረተልማት ዘርፍ ነባር የጠጠር መንገዶች ግንባታና አዲስ የመንገድ ከፈታ ምልከታ ከተደረገባቸው ዘርፎች ሲሆኑ ከተማዋ ካላት የቆዳ ስፋት አኳያ የመንገድ መሰረተልማት ተደራሽ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አበረታች መሆኑ ተነግሯል።

የስራ ሃላፊዎቹ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የምክር ቤት ህንጻ ግንባታ ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ህንጻው ሲጠናቀቅ የከተማዋን የቢሮና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ችግር የሚቀርፍና የግንባታ መስፈርቶችን አሟልቶ እየተገነባ መሆኑን ተመላክቷ ሲል የዘገበዉ የሚዛን አማን ከተማ የመንግሰት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *