


የቤሮ ወረዳ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን ውስጥ የሚገኝ ወረዳ ነው።
የቤሮ ወረዳ ከአዲስ አበባ በ709 ኪ/ሜ፣ ከሚዛን አማን በ142 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ወረዳው የሚታወቀው ይበልጥ በወርቅ ነው።
የቤሮ ወረዳ 12 ቀበሌዎች ያሉት ሲሆን አስራ ሁለቱም ቀበሌያት በማዕድንን ሀብቶችን የተጎናፀፉ ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ ምቹ የአየር ፀባይ መኖሩ ለምርትና ምርትታማነት ለማሳደግ ምቹ የእርሻ መሬት መኖሩ የመሬት አቀማመጧ በተፈጥሮ ቀዝቀዝ ያለና ምቹ የአየር ሁኔታ መኖሩ ለየት ያደርጋል ።
የቤሮ ወረዳ የተፈጥሮ ባለፀጋ ባለቤት ሲሆን የወርቅ፣ የእምነ በረድ፣ የከበረ ድንጋይ ባለቤት ከመሆኗ የተነሳ በወረዳ ውስጥ ከሁሉም ኢትዮጵያ ክፍል የሚመጡ ብዙዎች የሚኖሩባት ወረዳ ነው፡፡
ጋቢሳ፣ ሲያሊ፣ ሾላ፣ ገሰና እነዚህን የቤሮ ወረዳ ቀበሌዎች የሆኑት አነስተኛ የበረሃ ከተሞች በዋናነትም ወርቅ በብዛት የሚመራት ሲሆን እነዚህ አከባቢዎች በጸጋ ላይ ጸጋ የተቸሩ በረከታም የሆኑ አካባቢዎች ናቸው።
እነዚህ የበረሃ ከተሞች ዕልፍና ድንቃድንቅ የህይወት ስንክሳር አላቸው የካምፖቹን ገጠመኞች እንዲሁ በቁጭታ መተረክ አይቻልም በስፋት ለመተንተንም ሰፊ ጊዜን ይሻሉ።
በቤሮ ወረዳ ውስጥ ወርቅ በሁለት አይነት መንገድ ይመርታ የመጀመሪያው በባህላዊ መንገድ ሲሆን የሁለተኛው በልዩ አነስተኛ በማሽን ወርቅ ይመረታል ታዲያ ይህ አከባቢ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝባች ክልል የወርቅ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ የሚሸፈን አካባቢ መሆኑ ለየት ያደርገዋል።
መረጃው የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው፡፡
