የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች የምክክር መድረክ ተጀመረ

Spread the love

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አስተዳዳሪዎች የምክክር መድረክ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ ዛሬ ተጀምሯል።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው መድረኩ በልማት ትብብር፣ በጋራ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማሳደግ ላይ ሀሳብ ለመለዋወጥ ያለመ ነው።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍስሃ ሻውል፣ በመድረኩ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ ለድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች የጋራ መፍትሄ በማስቀመጥ የሁለቱን ወንድማማች ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የድንበር እና የውጭ ዜጎች ጉዳይ ዳይሬክተር አምባሳደር አንቲፓስ ኒዮክ በበኩላቸው፣ መድረኩ የጋራ ተጠቃሚነትን መንፈስ በማጎልበት የጋራ ጉዳዮችን ለመፍታት ጠቀሜታ እንዳለው መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *