




የካፋ ዞን ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃ እና ህብረት ስራ መምሪያ ምክትልና የተፈጥሮ ሀብትና አካባቢ ጥበቃ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተረፈ ወ/ገብርኤል በ2016 በጀት አመት በካፋ ዞን 74 ሚሊዬን በላይ የተለያዩ የደን እና የፍራፍሬ ችግኞችን በማዘጋጀት 69 ነጥብ 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ ሰፊ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡
በዞኑ እስከአሁን ከ50 ሚሊዮን በላይ ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን የተለያዩ ችግኞችን መትከል መቻሉንም የመምሪያ ምክትል ኃላፊ ገልፀዋል ።
እንደሀገር በአንድ ጀንበር 600 ሚሊየን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከ18 ሚሊዮን በላይ ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል በተያዘው መርሃግብር መሠረት በካፋ ዞን በአንድ ጀንበር 5 ሚሊዮን 2 መቶ 55 ሺህ ችግኝ ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ ተረፈ ወ/ገብርኤል ጠቁመዋል ፡፡
”ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ቃል በነሐሴ 17/2016 ዓ/ም የአንድ ጀምበር አርንጓዴ አሻራ ችግኝተ ተከላ መርሃ ግብር የጉድጓድ፣የችግኝ፣የቦታ ዝግጅት ስራዎችን ጨምሮ በቂ ዝግጅት መደረጉን ነው አቶ ተረፈ ወ/ገብርኤል የተናገሩት።
አሁን በዞኑ የሚተከሉ ችግኞች የአካባቢውን ስነ ምህደር ከመጠበቅ አኳያ ፋይዳ የጎላ መሆኑን የተናገሩት የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ ተረፈ ወ/ገብርኤል
የፍራፍሬ ችግኞቹ የስነ ምግብ ፍላጎትን ከማሟላት አልፈው ለአካባቢ ጥበቃ እና የኢኮኖሚ አቅም በማሳደግ የሚኖራቸው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ለአንድ ጀንበር ተከላ 60 ፐርሰንት የሚሆኑ ዘረፋ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ችግኞች፣ 40 ፐርሰንት የቀርከሃ እና ሌሎች የደን ዝሪያ ያላቸው የተለያዩ ችግኞች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል፡፡
ለዚህም በዞኑ የተለዩ 298 የተከላ ሳይቶች መኖራቸውንና 2 ሺህ 1 መቶ ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን አንስተዋል ።
እነዚህ ከተከላ ሳይቶች ውስጥ አንዱ የጎጀብ ተከላ ሳይት ሲሆን መረጃው ከፌደራል ጋር የተሳሰራ መሆኑንና በዚህም ተከላ ሳይት ከ100 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል ከ46 ሄክተር በላይ መሬት የተዘጋጀ እና 90 ሺህ በላይ ጉድጓድ መዘጋጀቱን አቶ ተፈረ ገልፀዋል ።
አሁን ላይ የዝግጅት ስራውን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን ያሉት ምክትል ኃላፊው በተከላውም ከ3 መቶ ሺህ በላይ የዞኑ ህዝብ ተሳታፊ እንደሚሆንና በአሁኑ ሰአት ችግኞቹ ወደተከላ ስፍራዎች በመጓጓዝ ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ለዚህም በበቂ ሁኔታ መላው ህብረተሰቡን ለተከላ እራሱን እንዲያዘጋጅ መደረጉንና የተለያዩ የክልል የዞንና የወረዳ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ጭምር እንደሚሳተፉ ገልፀዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራ ዋና ዓላማው ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት መሆኑን ያብራሩት አቶ ተረፈ ወ/ገብርኤል ከውበት እና ከጥላነት ባሻገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ብሎም ለዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚውሉ ችግኞች በየአካባቢው መተከል እንዳለባቸው በመጥቀስ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ ፕሮግራም ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
