rtrt

Spread the love

በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ የሀገር አቀፍ ዘመቻ አካል የሆነው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ ፣ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትንን ጨምሮ ሌሎች የክልል የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

መርሃ ግብሩ በሁሉም መዋቅሮች የተጀመረ ሲሆን በዞኑ ”ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መርሀ ግብር በአንድ ጀምበር 8.8 ሚሊዮን በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ችግኞች ለመትከል ዕቅድ ተይዟል።

በአንድ ጀምበር ተከላ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ችግኝ ለመትከል የየአከባቢው ነዋሪዎች በነቂስ በመወጣት ችግኝ እየተከሉ መሆኑን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *