የሸኮ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቲካሻ ቤንጊ”በቴፒ ማዕከል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ነው

Spread the love

ሸካ ዞን፤ ጥር 14/2018 (መ.ኮ.ጉ)የሸኮ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል የሆነው “ቲካሻ ቤንጊ”በሸካ ዞን ቴፒ ማዕከል በተለያዩ ማራኪ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅቦ በደመቀ ሁኔታ መከበር ጀምሯል።

“ቲካሻ ቤንጊ”ይቅርታና መተማመን የሚሰፍንበት፣ ግጭቶች በሽምግልና የሚፈቱበትና የአብሮነትና የሰላም እሴት ጎልቶ የሚገለጥበት የብሄረሰቡ ቱባ ባህል ነው።

“ቲካሻ ቤንጊ”ከአዝመራ መሰብሰብ በኋላ የሚከበር ታላቅ በዓል ሲሆን አሮጌውን ዘመን ተሸኝቶ አዲሱን ዓመት በተስፋ፣ በአንድነትና በምስጋና የሚቀበልበት በዓል ነው።

በበዓሉ ወቅት አዲሱ ምርት በጋራ ተቀምሶ ለፈጣሪ ምስጋና ይቀርባል፤ ይህም የብሔረሰቡን አንድነትና ባህላዊ እሴቶች የሚያጠናክር ቀደምት ትውፊት ነው።

የብሔረሰቡን ማንነት የሚገልጹ የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎችና ዜማዎች ለበዓሉ ልዩ ድምቀት ሰጥተውታል።

በበዓሉ ላይ የሸኮ ብሔረሰብ ተወላጆች፣ የክልልና የዞን የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው በዓሉን በደስታ እየታደሙ ይገኛሉ ሲል የሸካ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *