‎ክልል አቀፍ የባህል ስፖርቶችና የባህል ፌስቲቫል ውድድር የተሳካ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ

Spread the love

‎ከጥር 14 እስከ 19 በቦንጋ ከተማ ለሚካሄደው ክልል አቀፍ የባህል ስፖርቶች፤ ባህል ፌስቲቫልና የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ምዘና ውድድሩን አስመልክቶ የባለድርሻ አካላት መድረክ ተካሂዷል።

‎በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳዊት ደስታ ፌስቲቫሉ ከስፖርታዊ ውድድር ባሻገር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክር መድረክ እንደሆነ ገልፀዋል።

‎ከጥር 14 እስከ 19 በቦንጋ ከተማ በሚካሄደው ውድድር በ11 ልዩ ልዩ ባህላዊ ስፖርትና በ6 ዘመናዊ ስፖርት ዘርፎች ውድድር እንደሚካሄድ ገልፀው ከ633 በላይ ተሳታፊዎች በውድድሩ እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል።

‎ስፖርት በራሱ ሰላም በመሆኑ ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ሁሉም በትብብር መስራት እንደሚገባ የጠቆሙት አቶ ዳዊት በተለይ የፀጥታ አካላት ዳኞችና የስፖርት ማህበረሰብ በውድድሩ ወቅት የሚገጥሙ አለመግባባቶችን ቀድሞ የመፍታት ሀላፊነት ልወጡ ይገባል ብለዋል።

‎የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ተሳትፎና ውድድር ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ በየነ ቴቃ በበኩላቸው በውድድሩ በሀገር አቀፍ ተወዳዳሪ የሆኑ ወጣቶችና ታዳጊዎችን ለመለየት ያለመ በመሆኑ የስፖርት ድስፕልንና ስፖርታዊ ጨዋነትን ማስጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

‎በንጉሴ ወልደየስ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *