ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በክልላዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ የሚመክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ላይ የሚመክር፣ የፀጥታ ግብረሃይል መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ወቅታዊ ክልላዊ የፀጥታ ሁኔታዎችን የሚዳስስ ስነድ እና የፀጥታ ግብረሃይል ዕቅድ በክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊዎች እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

መድረኩ በክልሉ አስተማማኝና ዘላቂ ሠላም በማስፈን ሁለንተናዊ ክልላዊ እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የጋራ ተግባቦት ለመፈጠር ያለመ መኾኑንም ተመላክቷል።

በመድረኩ የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ተወካዮች፣ የፌደራል ፖሊስ ፈጥኖ ደራሽ አዛዦች እና በክልሉ የሁሉም ዞን አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ሌሎች የባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *