ህንግጫ ህዝባዊ መሠረት ይዞ እንዲከበርና በሚፈለገው ልክ እንዲያድግ ሁሉም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ ይገባል

Spread the love

ህንግጫ ህዝባዊ መሠረት ይዞ እንዲከበርና በሚፈለገው ልክ እንዲያድግ ሁሉም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ ይገባል፦አቶ ታከለ ተስፉ

የኮንታ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ህንግጫ’በዓል ዕርቀ- ሰላም የሚወርድበት፣የተራራቁት የሚሰበሰቡት ፣ጎዶሎዉ ሞልቶ በሙላት የመሻገር አስተምሮ፣ የአብሮነት እና የአንድነት መገለጫ ነዉ ሲሉ የኮንታ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ታከለ ተስፉ ገለጹ።

የኮንታ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ የ”ህንግጫ” በዓል አካል የሆነዉ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ፓናል ውይይት በዞኑ ዋና ከተማ አመያ እየተካሄደ ነዉ።

በፓናል ውይይቱ ንግግር ያደረጉት የኮንታ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ታከለ ተስፉ ፤የኮንታ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ህንግጫ’በዓል ዕርቀ- ሰላም የሚወርድበትነዉ። የተራራቁት የሚሰበሰቡት ፣ጎዶሎዉ ሞልቶ በሙላት የመሻገር አስተምሮ፣ የአብሮነት እና የአንድነት መገለጫ የሆነ የብሔረሰቡ ከአሮጌዉ ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገሪያ በዓል ነዉ።

ህንግጫ ለጋራ ሀገር ልማት፣ አብሮነትና ወንድማማችነት ከሚኖረዉ ጠቀሜታ ባሻገር ለኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊ እና ባህላዊ ውህደት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ ነዉ።

ህንግጫ ህዝባዊ መሠረት ይዞ እንዲከበርና በሚፈለገው ልክ እንዲያድግ ሁሉም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በዓሉ አንድ ደረጃ አድጎ እንዲከበር እና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በፓናል ውይይት እንዲጎለብት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ በመሆናቸው ለዚህ ስራ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነዋል።

ህንግጫ የኮንታ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ ባህላዊ ይዘቱንና ትውፈቱን ሳይለቅና ሳይደበዝዝ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ እንዲተላለፍ የድሮ አባቶች ጠንካራ መሠረት መጣሉን የኮንታ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ ደምሴ አስታውሰዋል።

ኮንታ በርካታ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ባህል ፣ታርክ እና እሴቶች ባለቤት ነው ያሉት አቶ አበበ ከዘመን ወደ ዘመን ከትውልድ ወደ ትውልድ ባህላዊ ይዘቱን ሳየለቅ ሲከበር የቆየዉን የብሔረሰቡ ዘመን መለወጫ ህንግጫ የዚሁ አካል ነዉ።

ህንግጫ ምንም ከኃይማኖት አስተምሮ ጋር ግኝኑነት የለለዉ የብሔረሰቡ የዘመን መለወጫ በመሆኑ በዓልን የአሁን ትውልድ በመጠበቅ እና በመንከባከብ እንዲሁም በማልማት ለቀጣይ ትዉልድ እንዲተላለፍ በአብኩሮ መሥራት ይጠበቅበታልም ብለዋል።

በሲምፖዚየሙ ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢ የሚገኙ የብሔረሰቡ ተወላጆችና ምሁራን፣ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የብሔረሰቡ ታሪክና ባህል ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች እየቀረቡ ነዉ።

በፍቅር ከበደ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *