




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት እና የሁሉም ዞኖች ወጣቶች ክንፍ እና ሌሎች የመንግስት አካላት በምዕራብ ኦሞ ዞን በሱሪ ወረዳ ኪብሽ ከተማ ተገኝተው ለአርብቶ አደር ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
በመርሃ ግብሩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት ሰዒድ ኢብራሂም የፓርቲያችንን ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ በመከተል የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን የዘውትር ተግባራችን ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በጎ ፈቃደኝነት ከበጎ ህሊና የሚመነጭ ፣ በመስጠት የሚገኝ የመንፈስ እርካታ በመሆኑ ድንበር የለውም
ያሉት ኃላፊው አቅመ ደካማን፣ አረጋዊያንን እና የተቸገሩ ወገኖችን መርዳት መደገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።
የአርብቶ አደር ተማሪዎች ለመደገፍ በቅንጅት እንሰራለን ብልዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ሃላፊ አቶ ግርማ በሻ ትምህርት ላይ መስራት በሀገር ግንባታ ላይ መስራት ከመሆኑም ጋር ተያይዞ የመማሪያ ቁሳቁሶች ለተማሪዎች አስፈላጊ መሆኑ ተናግሯል።
የአርብቶ አደር ተማሪዎች በትምርት ላይ ንቁ ተሳትፎና ውጤታማ እንዲሆኑ መደገፍና ማበረታታት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የዞኑ ወጣቶች ክንፍ ሃላፊ አቶ ፀጋለም ሳሙኤል የወጣቶች ተጠቃሚነት ላይ ከወትሮው ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑ ገልጸዋል።
በበጎ አድራጎት የሚሰሩ ሥራዎች ላይ ሁሉም የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ባርዱላ ኦሌጱሴኒ አክለው በወረዳ በባለፈው ጊዜያት በተሰራ የፀጥታ ሥራዎች ከፍተኛ መሻሻል መታየቱ አውስተው ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሥራዎች በሁሉም ትምህርት ቤቶች መጀመራቸውን ተናግሯል።
በዚህ የተደረገው አበረታች መሆኑ ጠቅሶ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብልዋል በመልዕክታቸው።
