የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሴክተር መስሪያቤቶች የዕቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ነው

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የሴክተር መ/ቤቶች የዕቅድ አፈፃፀም የግምገመ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነው።

የመድረኩ ዋና ዓላማው የክልል ሴክተር መስሪያቤቶች በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ሩብ አመት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም በጋራ በመገምገም ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ለመድረስ ያለመ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሄም ዳንኤል መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት ያልተከናወኑ ቀሪ ተግባራት በማካተት የክልሉ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በማቀድ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመገምገም ወደ ስራ የተገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይህም ዕቅድ ከ10 ዓመቱ መሪ ዕቅድ የተቀዳ መሆኑን ያነሱት የቢሮው ኃላፊዋ ከበጀት ዓመት ዕቅዱ መነሻ በዚህኛው ሩብ ዓመት ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በሴክተር መስሪያ ቤቶች የተከናወኑ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ኃላፊዋ አክለውም በ2018 በጀት አመት በአንደኛ ሩብ አመት በአንዳንድ ተቋማት ከዝግጅት ምዕራፍ ባሻገር በርካታ በጥረት የተሰሩ ተግባራት መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይህ ክልላዊ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት የኢኮኖሚ ዘርፍ ተቋማት የዕቅድ አፈፃፀም እየቀረበ ሲሆን መድረኩ ዛሬን ጨምሮ ለሚቀጥሉት ለተከታታይ 5 ቀናት ከተለያዩ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት የሚቀጥል ይሆናል።

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *