






በመድረኩ በ19ኛዉ የብሔር ብሔረሰቦች በዓል አከባበር ወቅት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ክፍተቶችንም ለማረም የሚያስችል መነሻ ሰነድ ቀርቦ ምክክር ተደርጎበታል።
መድረኩን የመሩት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታና የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መቱ አኩ እንደገለጹት አምና ላይ በበዓሉ አከባበር ወቅት የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ከማስቀጠልም በተጠማሪ ዘንድሮ ላይ በአካባቢ ጽዳት ፣ በደም ልገሳና በተለያዩ በጎ ተግባራት በአደባባይ በደማቅ ለማክበር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከወዲሁ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርትን በአግባቡ ለሚመለከተዉ ማቅረብ እንደሚያስፈልግ እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራርን እስከታችኛዉ መዋቅር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ በተሳካ ሁኔታ የዘንድሮዉን በዓል ለማክበር እንዲቻል ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን የሚጠበቅባቸዉን እንደሚሰሩ ጠቁመዋል
የዘንድሮዉ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን “ዴሞክራሲያው መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ በታችኛዉ መዋቅር ከህዳር 1 እስከ 18 ቀን እንደሚከበርና በክልል ደረጃ ደግሞ በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ህዳር 18 እስከ 20 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት እንደሚከበርም ተገልጿል ሲል ማሻ ኤፍኤም ዘግቧል።
